La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 47:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴ​ፍም የግ​ብ​ፅን ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነሆ ዛሬ እና​ን​ተ​ንና ምድ​ራ​ች​ሁን ለፈ​ር​ዖን ገዝ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ና​ንተ ዘር ውሰ​ዱና ምድ​ሪ​ቱን ዝሩ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ ዛሬ እናንተንም መሬታችሁንም ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁና ይህን ዘር ወስዳችሁ በመሬት ላይ ዝሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “እነሆ ዛሬ እናንተንና ምድራችሁን ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁ፥ ዘር ውሰዱና ምድሪቱን ዝሩ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሴፍ ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፥ እንግዲህ እናንተንና መሬታችሁን ለፈርዖን ስለ ገዛሁ ዘር ውሰዱና በመሬታችሁ ላይ ዝሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ እነሆ ዛሬ እናንተንና ምድራችሁን ለፈርዖን ገዝቻችኍለሁ ዘር ውሰዱና

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 47:23
15 Referencias Cruzadas  

ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው።


እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በም​ድር ላይ ራብ የሆ​ነ​በት ነውና፤ የማ​ይ​ታ​ረ​ስ​በ​ትና የማ​ይ​ታ​ጨ​ድ​በት አም​ስት ዓመት ገና አለ።


ዮሴፍ የካ​ህ​ና​ትን ምድር ብቻ አል​ገ​ዛም፤ ፈር​ዖን ለካ​ህ​ናቱ ድርጎ ይሰ​ጣ​ቸው ነበ​ርና፥ ፈር​ዖ​ንም የሰ​ጣ​ቸ​ውን ድርጎ ይበሉ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን አል​ሸ​ጡም።


በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”


እንደ አም​ላ​ካ​ችን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር።


ዋሊያ ወደ ውኃ ምን​ጮች እን​ደ​ሚ​ና​ፍቅ፥ እን​ዲሁ ነፍሴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትና​ፍ​ቃ​ለች።


ስንዴውን የሚያደልብ ለአሕዛብ ይተወዋል። በረከት ግን በሚሰጥ ሰው ራስ ላይ ነው።


ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል። በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።


ጻድቃን ለብዙ ዓመት በብልጽግና ይኖራሉ፤ ዐመፀኞች ግን ፈጥነው ይጠፋሉ።


ይህ ወይም ያ ማና​ቸው እን​ዲ​በ​ቅል ወይም ሁለቱ መል​ካም እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምና በማ​ለዳ ዘር​ህን ዝራ፥ በማ​ታም እጅ​ህን አት​ተው።


ብዙ ዝና​ምና በረዶ ከሰ​ማይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ፥ ምድ​ርን እን​ደ​ሚ​ያ​ረ​ካት፥ ታበ​ቅ​ልና ታፈ​ራም ዘንድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጋት፥ ዘርን ለሚ​ዘራ፥ እህ​ል​ንም ለም​ግብ እን​ደ​ሚ​ሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ፥


“እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?


እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰ​ጣል፤ እህ​ል​ንም ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ያበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ የጽ​ድ​ቃ​ች​ሁ​ንም መከር ያበ​ጃል።