እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን እጅግ ቈስለው ሳሉ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ተደፋፍረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፤
ዘፍጥረት 42:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ከእነርሱ ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ደግሞም ወደ እነርሱ ተመልሶ ተናገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ወስዶ በፊታቸው አሰረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደ እነርሱ ተመልሶ እንደ ገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዐይናቸው እያየ አሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደ እነርሱ ተመልሶ እንደገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዐይናቸው እያየ አሰረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ ከእነርሱ ነጠል ብሎ አለቀሰ፤ እንደገናም ወደ እነርሱ ተመልሶ አነጋገራቸውና ስምዖንን ከመካከላቸው ወስዶ በፊታቸው አሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ዘወር ብሎ አለቀሰ ደግሞም ወደ እነርሱ ተመልሶ ተናገራቸው ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ወሰዶ በፊታቸው አሰረው። |
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን እጅግ ቈስለው ሳሉ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ተደፋፍረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፤
አምላኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገስን ይስጣችሁ፤ ያን ወንድማችሁንና ብንያምንም ይመልስላችሁ፤ እኔም ልጆችን እንዳጣሁ አጣሁ።”
እርሱም አላቸው፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ አምላካችሁ የአባቶቻችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁንስ መዝኜ ተቀብያለሁ።”
ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው።
አንዱ የአካል ክፍል ቢታመም ከእርሱ ጋር የአካል ክፍሎች ሁሉ ይታመማሉ፤ አንዱ የአካል ክፍል ደስ ቢለውም የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው።