ዘፍጥረት 38:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ እጁን በመለሰ ጊዜ እነሆ፥ ወንድሙ ወጣ፤ እርስዋም፥ “ለምን ጥሰህ ወጣህ? ስትል ስሙን ፋሬስ” ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እጁን በመለሰው ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ተወለደ፤ አዋላጂቱም ሴት “እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ስለዚህ የመጀመሪያው ልጅ ስም “ፋሬስ” ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ እጁን በመለሰ ጊዜ እነሆ ወንድሙ ወጣ፤ እርስዋም፦ ለምን ጥስህ ወጣህ? አለች፤ |
የይሁዳም ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስሮም፥ ይሞሔል፤
ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ፥ የሰፋጥያስ ልጅ፥ የሰማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ አታያ፤