ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ዘፍጥረት 37:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቹም፥ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆነን ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቹም፣ “ለካስ በላያችን ለመንገሥ ታስባለህና! ለመሆኑ አንተ እኛን ልትገዛ!” አሉት፤ ስለ ሕልሙና ስለ ተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቹም፦ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቹም “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን?” ብለው ጠየቁት። ስላየው ሕልምና ስለ ተናገረው ቃል ከበፊቱ ይበልጥ ጠሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቹም፦ በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን? አሉት። እንደ ገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ ይልቁን ጠሉት። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ደግሞም ሌላ ሕልምን አየ፤ ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም እንዲህ ነው፦ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ይሰግዱልኝ ነበር።”
ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እንዲህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ በፊትህ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ፤ እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ፤ አንተ ከፈርዖን ቀጥለህ ነህና።
የአባትህና የእናትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ይበልጣሉ፤ ዘለዓለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኀያላን ናቸው፤ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ራስ አናት ላይ ይሆናሉ።
ወንድሙን የሚበድለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአልን?” ብሎ ፈራ።
ጌታችን ኢየሱስም ተመለከተና እንዲህ አላቸው፤ “ግንበኞች የናቁአት ድንጋይ እርስዋ የማዕዘን ራስ ሆነች፥ የሚለው ጽሑፍ ምንድነው?
“በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አድርጎሃል? ብለው የካዱትን ያን ሙሴን በቍጥቋጦው መካከል በታየው በመልአኩ እጅ እርሱን መልእክተኛና አዳኝ አድርጎ እግዚአብሔር ላከው።
በየወቅቱም ከምድሪቱ ምላት፥ በቍጥቋጦው ውስጥ ከነበረው በረከት፥ በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በከበረው በእርሱ ራስ ላይ ይውረድ።
የእግዚአብሔርን ልጅ የከዳ፥ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?
ታላቅ ወንድሙም ኤልያብ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ ኤልያብም በዳዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂቶች በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው? እኔ ኵራትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል” አለው።
ሳኦልም እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር ሳኦልን አስከፋው፤ እርሱም፥ “ለዳዊት ዐሥር ሺህ ሰጡት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ሰጡኝ፤ ከመንግሥት በቀር ምን ቀረበት?” አለ።