ዘፍጥረት 36:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም ሞተ፤ በእርሱ ፈንታም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤላዕ ሞተ፥ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ዮባብ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤላዕ በሞተ ጊዜ የቦጽራ አገር ተወላጅ የዘራሕ ልጅ ዮባብ በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም ሞተ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ ኢዮባብም ሞተ |
እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰደቢያና መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘለዓለም ባድማ ይሆናሉ።
እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመለከታል፤ ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኀያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።
ያዕቆብ ሆይ፥ ሁልንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፥ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፥ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።