አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ።
ዘፍጥረት 35:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእጃቸው ያሉትንም እንግዶች አማልክት ሁሉ፥ በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፤ ያዕቆብም በሴቄም አጠገብ ካለችው ዛፍ በታች ቀበራቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጕትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በእርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ አምጥተው ለያዕቆብ ሰጡት፤ እንዲሁም በየጆሮአቸው አድርገውት የነበረውን ጒትቻ ሁሉ አውልቀው ሰጡት፤ እርሱም ሁሉንም ወሰደና በሴኬም አጠገብ በነበረው የወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእጃቸው ያሉትንም እንግዶችን አማልክት ሁሉ በጆሮአችው ያሉትን ጕትቾች ለያዕቆብ ሰጡት ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የአድባር ዛፍ በታች ቀበራቸው ተነሥተውም ሄዱ፤ |
አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ።
ተነሡና ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ቀን ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው፥ ከመከራም አድኖ ላሻገረኝ ለእግዚአብሔር መሠውያን እንሥራ።”
እስራኤልም ከሴቄም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም መፍራት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእስራኤልንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።
የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ ፈጨው፤ አደቀቀውም፤ በውኃም ላይ በተነው፤ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣቸው።
በዚያም ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል።
በብርም ወደ ተለበጡ፥ በወርቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖታቱ እንሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያንጊዜ እንደ ትቢያ የደቀቁ ይሆናሉ፤ እንደ ውኃም ይደፈርሳሉ፤ በእነርሱም ጥራጊዎችን ይጥሉባቸዋል።
እኔን ረስታ ወዳጆችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም የሠዋችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ ከእነርሱም የተሠራባቸውን ብርንና ወርቅን፥ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትበድልበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፤ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የአማልክቶቻቸውንም ምስል በእሳት አቃጥሉ።
የሰቂማም ሰዎች ሁሉ፥ የመሐሎንም ቤት ሁሉ ተሰበሰቡ፤ ሄደውም በሰቂማ በዐምዱ አጠገብ ባለው የወይራ ዛፍ በታች አቤሜሌክን አነገሡ።