Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በዚ​ያም ቀን ሰው ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ያበ​ጁ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቹን ለፍ​ል​ፈ​ልና ለሌ​ሊት ወፍ ይጥ​ላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በዚያ ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በዚያን ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፤ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሰዎች ይሰግዱላቸው ዘንድ በእጃቸው የሠሩአቸውን የብርና የወርቅ ምስሎች ለፍልፈሎችና ለሌሊት ወፎች እየጣሉላቸው ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 2:20
17 Referencias Cruzadas  

በብ​ርም ወደ ተለ​በጡ፥ በወ​ር​ቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖ​ታቱ እን​ሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያን​ጊዜ እንደ ትቢያ የደ​ቀቁ ይሆ​ናሉ፤ እንደ ውኃም ይደ​ፈ​ር​ሳሉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ጥራ​ጊ​ዎ​ችን ይጥ​ሉ​ባ​ቸ​ዋል።


በዚ​ያም ቀን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እጆ​ቻ​ቸው የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይጥ​ላሉ።


ተመ​ል​ሰ​ውም ከጥ​ላው ሥር ይቀ​መ​ጣሉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራሉ፤ ከእ​ህ​ሉም የተ​ነሣ ይጠ​ግ​ባሉ፤ እንደ ወይ​ንም አረግ ያብ​ባሉ ፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ወይን ይሆ​ናል።


ወር​ቁ​ንና ብሩን ከኮ​ሮጆ የሚ​ያ​ወ​ጡና በሚ​ዛን የሚ​መ​ዝኑ እነ​ርሱ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን ይቀ​ጥ​ራሉ፤ እር​ሱም ጣዖት አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ዋል፤ ለዚ​ያም ይጐ​ነ​በ​ሱ​ለ​ታል፤ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ት​ማል።


ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰ​ባ​በረ፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራ​ዊ​ትና እን​ስ​ሳም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ እንደ ፋን​ድ​ያም ሸክም የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና አያ​ነ​ሡ​አ​ቸ​ውም።


ሸመላ፥ ሳቢሳ በየ​ወ​ገኑ፤ ጅን​ጅ​ላቴ ወፍ፥ የሌ​ሊት ወፍ።


ያን​ጊ​ዜም ተራ​ሮ​ችን ‘በላ​ያ​ችን ውደቁ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ሰው​ሩን’ ይሉ​አ​ቸ​ዋል።


በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውና ጣቶ​ቻ​ቸው በሠ​ሩ​አ​ቸው የእ​ጃ​ቸው ሥራ​ዎች አይ​ተ​ማ​መ​ኑም፤ ለር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም ዛፎ​ችን አይ​ቈ​ር​ጡም።


እን​ጨት ጠራቢ በሠ​ራው ምስል፥ ወይስ አን​ጥ​ረኛ መትቶ በሠ​ራው ወርቅ፥ በወ​ር​ቅም ለብጦ በሠ​ራው ምስል ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ች​ሁን?


ብራ​ቸ​ውን በጎ​ዳ​ና​ዎቹ ላይ ይጥ​ላሉ፤ ወር​ቃ​ቸ​ውም ይረ​ክ​ሳል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት ቀን ብራ​ቸ​ውና ወር​ቃ​ቸው አያ​ድ​ና​ቸ​ውም። እርሱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው እን​ቅ​ፋት ሆኖ​አ​ልና ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አያ​ጠ​ግ​ቡም፤ ሆዳ​ቸ​ው​ንም አይ​ሞ​ሉም።


ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በል፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ንስሓ ግቡ፤ ከበ​ደ​ላ​ች​ሁም ተመ​ለሱ፤ ፊታ​ች​ሁ​ንም ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ መልሱ።


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


በእ​ጃ​ቸው ያሉ​ት​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ሁሉ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም ያሉ​ትን ጉት​ቾች ለያ​ዕ​ቆብ ሰጡት፤ ያዕ​ቆ​ብም በሴ​ቄም አጠ​ገብ ካለ​ችው ዛፍ በታች ቀበ​ራ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።


ለመ​ፈ​ለግ ጊዜ አለው፥ ለማ​ጥ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ጠ​በቅ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጣ​ልም ጊዜ አለው፤


በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios