Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 32:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የሠ​ሩ​ት​ንም ጥጃ ወስዶ በእ​ሳት አቀ​ለ​ጠው፤ ፈጨው፤ አደ​ቀ​ቀ​ውም፤ በው​ኃም ላይ በተ​ነው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አጠ​ጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ያበጁትን ጥጃ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ከዚያም ዱቄት እስኪሆን ፈጨው፤ በውሃ ላይ በተነው፤ እስራኤላውያንም እንዲጠጡት አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የሠሩትን ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እስኪደቅም ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲጠጡት አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እነርሱ የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ አቀለጠው፤ እስኪልም ድረስ አደቀቀውና ከውሃ ጋር ደባልቆ የእስራኤል ሕዝብ እንዲጠጣው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 32:20
10 Referencias Cruzadas  

ስለ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትም ኀጢ​አት የጥ​ጃ​ውን ምስል ወሰ​ድሁ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ል​ሁት፤ አደ​ቀ​ቅ​ሁ​ትም፤ እንደ ትቢ​ያም እስ​ኪ​ሆን ድረስ ፈጨ​ሁት፤ እንደ ትቢ​ያም ሆነ፤ ትቢ​ያ​ው​ንም ከተ​ራ​ራው በሚ​ወ​ርድ ወንዝ ጨመ​ር​ሁት።


ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።


ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ።


ደግ​ሞም በቤ​ቴል ኮረ​ብታ የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳተ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ያሠ​ራ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገጃ፥ ይህ​ንም መሠ​ዊ​ያና መስ​ገጃ አፈ​ረሰ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱ​ንም አቃ​ጠ​ለው።


የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ጣዖት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ወደ ቄድ​ሮን ፈፋ አወ​ጣው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፥ ትቢ​ያ​ው​ንም በሕ​ዝብ መቃ​ብር ላይ ጨመ​ረው።


የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ።


ነገር ግን እን​ዲህ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቍረጡ፥ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስል በእ​ሳት አቃ​ጥሉ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።


የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ጣዖ​ታ​ትን ስለ ሠራች እና​ቱን ሐናን እቴጌ እን​ዳ​ት​ሆን ሻራት፤ አሳም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱን አስ​ቈ​ረ​ጠው፥ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ በእ​ሳት አቃ​ጠ​ለው።


የበ​ዓ​ሊ​ም​ንም መሠ​ዊ​ያ​ዎች በፊቱ አፈ​ረሰ፤ በላ​ዩም የነ​በ​ሩ​ትን ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ችን ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ቈረጠ፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች ሰባ​በረ፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፤ ይሠ​ዉ​ላ​ቸው በነ​በ​ሩት ሰዎች መቃ​ብ​ርም ላይ በተ​ና​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios