መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።
ዘፍጥረት 32:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የላካቸው መልእክተኞችም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ሊቀበልህ በመምጣት ላይ ነው፤ አራት መቶ ሰዎችም ዐብረውት አሉ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፥ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው መጡና “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ። |
መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።
አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።
ያዕቆብም እጅግ ፈራ፤ የሚያደርገውንም አጣ። ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች ላሞችንም፥ ግመሎችንም፥ በጎችንም ሁለት ወገን አድርጎ ከፈላቸው፤
ያዕቆብም ዐይኑን አነሣ፤ እነሆም፥ ዔሳውን ሲመጣ አየው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ዕቁባቶቹ አደረጋቸው፤
ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን?” አለ። እርሱም፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘቴ ይበቃኛል” አለ።
ዔሳውም፥ “ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እርሱም፥ “በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ያደረግሁልህ ነው” አለ።
ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ይሆናል።
እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።
ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።
እርስዋም፥ “ባርያህ በፊትህ ሞገስን አገኘች” አለችው። ሴቲቱም መንገድዋን ሄደች፤ ወደ ቤትዋም ገባች፤ ከባሏም ጋር በላች፤ ጠጣችም ፤ ፊቷም ከዚያ በኋላ አዘንተኛ መስሎ አልታየም።