Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 32:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፥ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ሊቀበልህ በመምጣት ላይ ነው፤ አራት መቶ ሰዎችም ዐብረውት አሉ” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው መጡና “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 32:6
14 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ ተመለከተም፥ እነሆም ዔሳው እየመጣ ነበር፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ። ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም አገልጋዮች አደረጋቸው።


ከአንበሳ ፊት ሲሸሽ ድብ እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።


ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፥ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።


“ዔሳው መጥቶ አንዱን ወገን የመታ እንደሆነ የቀረው ወገን ያመልጣል።” ብሎም አሰበ።


ያዕቆብም እጅግ ፈራ ተጨነቀም፤ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች፥ መንጎችን እና ከብቶችን ግመሎችንም፥ በሁለት ወገን ከፈላቸው፥


መንጎቹንም ሁሉ፥ ያፈራውን ንብረት ሁሉ፥ ፓዳን-ኣራም ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።


እርሱም፥ “ያገኘሁት ይህ ሁሉ ጓዝ ምንህ ነው?” አለ። እርሱም፥ “በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው” አለ።


ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን” አለ። እርሱ ግን፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘት ይበቃኛል” አለ።


ሴኬምም አባትዋንና ወንድሞችዋን እንዲህ አለ፥ “በፊታችሁ ሞገስን ባገኝ የምትሉኝን እሰጣለሁ።


እነርሱም፦ “አንተ ሕይወታችንን አተረፍክ፥ ጌታችንን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ፥ ለፈርዖንም ባርያዎች እንሆናለን” አሉት።


ሞአባዊቱም ሩት ናዖሚንን፦ “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው ተከትዬ እህል ለመቃረም ወደ እርሻ ልሂድ” አለቻት። እርሷም፦ “ልጄ ሆይ፥ ሂጂ” አለቻት።


እርሷም፦ “ጌታዬ ሆይ፥ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኸኛልና፥ የባርያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ” አለችው።


እርሷም፥ “አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ታግኝ” አለች፤ ከዚያም ተነሥታ መንገዷን ቀጠለች፤ ምግብም በላች፤ በፊቷም ገጽ ኀዘን መታየቱ ቆመ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios