ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ “ከእንግዲህ ወዲህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፤ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው።
ዘፍጥረት 30:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም፥ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወደድኛል ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ ዐድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት፣ ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል”። አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም፦ እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው። |
ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ “ከእንግዲህ ወዲህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፤ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው።
ልያም፥ “ባሌን መውሰድሽ አይበቃሽምን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠቻትም።
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ! በሕዝብ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፤ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።
ሳኦልም አላቸው፥ “የንጉሥን ጠላቶች ይበቀል ዘንድ ከመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይሻም ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት” አላቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍልስጥኤማውያን እጅ ይጥለው ዘንድ አስቦ ነው።