Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ባር​ቅም ዛብ​ሎ​ን​ንና ንፍ​ታ​ሌ​ምን ወደ ቃዴስ ጠራ​ቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ወጡ፤ ዲቦ​ራም ከእ​ርሱ ጋር ወጣች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚያም ባርቅ የዛብሎንንና የንፍታሌምን ሰዎች ወደ ቃዴስ ጠራቸው፤ ዐሥር ሺሕ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም ዐብራው ሄደች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ባራቅ ለዛብሎንና ለንፍታሌም ሰዎች ጥሪ አስተላለፈ፤ ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም አብራው ሄደች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ባራቅም የንፍታሌምንና የዛብሎንን ነገዶች ወደ ቃዴስ አስጠራ፤ ከእነርሱም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም አብራው ዘመተች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ባርቅም ዛብሎንንና ንፍታሌምን ወደ ቃዴስ ጠራቸው፥ አሥር ሺህም ሰዎች ተከትለውት ወጡ፥ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ወጣች።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 4:10
9 Referencias Cruzadas  

በከ​ተ​ማ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት የከ​ተ​ማው ሰዎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ችም ኤል​ዛ​ቤል እን​ዳ​ዘ​ዘ​ቻ​ቸ​ውና ወደ እነ​ርሱ በተ​ላ​ከው ደብ​ዳቤ እንደ ተጻ​ፈው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ከሕ​ያ​ዋን መጽ​ሐፍ ይደ​ም​ሰሱ፥ ከጻ​ድ​ቃ​ንም ጋር አይ​ጻፉ።


እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​ህም ሕዝብ ሁሉ ከዚ​ያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወ​ር​ዳሉ፤ ለእ​ኔም ይሰ​ግ​ዳሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ እወ​ጣ​ለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።


ዲቦ​ራም ባር​ቅን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይሄ​ዳል” አለ​ችው። ባር​ቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ከታ​ቦር ተራራ ወረደ።


ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤


የይ​ሳ​ኮ​ርም አለ​ቆች ከዲ​ቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳ​ኮ​ርም እንደ ባርቅ ነበረ፤ ከእ​ግሩ በኋላ ወደ ሸለ​ቆው ቸኮሉ፤ በሮ​ቤል ፈሳ​ሾች አጠ​ገብ ብዙ የልብ ማመ​ን​ታት ነበረ።


ዛብ​ሎን ነፍ​ሱን ወደ ሞት ያሳ​ለፈ ሕዝብ ነው፤ ንፍ​ታ​ሌ​ምም በሀ​ገሩ ኮረ​ብታ ላይ ነው።


ወደ ምና​ሴም ነገድ ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ሱም ከኋ​ላው ሆኖ ጮኸ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ አሴ​ርና ወደ ዛብ​ሎን ወደ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊቀ​በ​ሉ​አ​ቸው ወጡ።


አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos