እግዚአብሔርም አለው፥ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?”
ዘፍጥረት 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አዳምን አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ከአዘዝሁህ ከዚያ ዛፍም በልተሃልና ምድር በሥራህ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዳምንም እንዲህ አለው፤ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ፣ ‘ከርሱ አትብላ’ ብዬ ያዘዝሁህን ዛፍ በልተሃልና፣ “ከአንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ምግብህን ጥረህ ግረህ ከርሷ ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዳምንም አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም ከእርሱ በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርሷ ትበላለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዳምም አለው፤ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፤ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ |
እግዚአብሔርም አለው፥ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?”
ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ፥ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኋችሁ፤ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለሙን ድል ነሥቼዋለሁና።”
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።