Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 5:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዘመኑ ሁሉ በጨ​ለማ በል​ቅ​ሶና በብዙ ብስ​ጭት በደ​ዌና በኀ​ዘን ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በብዙ ጭንቀት፣ መከራና ብስጭት፣ ዘመኑን ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይበላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ቢኖር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ሲበላና ሲጠጣ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ሲለው ነው፥ ይህ እድል ፈንታው ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዕድሜውንም የሚፈጽመው ጨለማ በወረሰው ሕይወት፥ በሐዘን፥ በሚያስጨንቅ ሐሳብ፥ በብስጭትና በሕመም ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዘመኑን ሁሉ በጨለማ በኀዘን በብስጭት በደዌና በቍጣ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 5:17
21 Referencias Cruzadas  

የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ።


ሁል​ጊ​ዜም አይ​ቀ​ሥ​ፍም፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ቈ​ጣም።


ሌላ​ውም ሰው መል​ካ​ምን ነገር ከቶ ሳይ​በላ በተ​መ​ረ​ረች ነፍሱ ይሞ​ታል።


ነገር ግን የን​ዕ​ማን ለምጽ በአ​ን​ተና በዘ​ርህ ላይ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ” አለው። እንደ በረ​ዶም ለም​ጻም ሆኖ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።


እነ​ር​ሱም፥ “አንድ ሰው ሊገ​ና​ኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካ​ችሁ ንጉሥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ የላ​ክህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ስለ​ዚህ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በሉት አለን” አሉት።


አካ​ዝ​ያ​ስም በሰ​ማ​ርያ በሰ​ገ​ነቱ ላይ ሳለ በዐ​ይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ጠይቁ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊጠ​ይ​ቁ​ለት ሄዱ።


ሴት​የ​ዋም፥ “አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በማ​ድጋ ካለው ከእ​ፍኝ ዱቄት በማ​ሰ​ሮም ካለው ከጥ​ቂት ዘይት በቀር እን​ጀራ የለ​ኝም፤ እነ​ሆም፥ ጥቂት እን​ጨት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ ሄጄም ለእ​ኔና ለልጄ እጋ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በል​ተ​ነ​ውም እን​ሞ​ታ​ለን” አለ​ችው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ምን አለው፥ “የሚ​ስ​ት​ህን ቃል ሰም​ተ​ሃ​ልና፥ ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ከአ​ዘ​ዝ​ሁህ ከዚያ ዛፍም በል​ተ​ሃ​ልና ምድር በሥ​ራህ የተ​ረ​ገ​መች ትሁን፤ በሕ​ይ​ወት ዘመ​ን​ህም ሁሉ በድ​ካም ከእ​ር​ስዋ ትበ​ላ​ለህ፤


መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።


ዘመኑ ሁሉ መከራ፥ ቍጣም፥ ቅሚ​ያም ነው፤ ልቡም በሌ​ሊት አይ​ተ​ኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


ዐይ​ኖቼ ከፈ​ለ​ጉት ሁሉ አላ​ጣ​ሁም፥ ልቤ​ንም ከደ​ስታ ሁሉ አል​ከ​ለ​ከ​ል​ሁ​ትም፤ ልቤ በድ​ካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበ​ርና፤ ከድ​ካ​ሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋን​ታዬ ሆነ።


ለሰው ከመ​ብ​ላ​ትና ከመ​ጠ​ጣት በድ​ካ​ሙም ለሰ​ው​ነቱ መል​ካም ነገር ከሚ​ያ​ሳ​ያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።


በመ​ል​ካም ቀን ደስ ይበ​ልህ ፤ በክ​ፉም ቀን ተመ​ል​ከት፤ ሰው ከእ​ርሱ በኋላ መር​ምሮ ምንም እን​ዳ​ያ​ገኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ንም ያንም እን​ደ​ዚያ ሠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios