ዘፍጥረት 29:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ራሔልን ሳማት፤ ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ያዕቆብ ራሔልን ሳማት፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ራሔልን ሳማት፥ ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ራሔልን ሳማት፤ ከደስታውም ብዛት የተነሣ አለቀሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ራሔልን ሳማት ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። |
ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የአጎቱን የላባን በጎች በአየ ጊዜ ቀረበ፤ ከጕድጓዱም አፍ ድንጋዩን አነሣ፤ የአጎቱን የላባን በጎችም አጠጣ።
ላባም የእኅቱን የርብቃን ልጅ የያዕቆብን ስም በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው።
እግዚአብሔርም አሮንን አለው፥ “ሄደህ በምድረ በዳ ሙሴን ተገናኘው፤” ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፤ እርስ በርሳቸውም ተሳሳሙ።