ዘፍጥረት 27:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ እኔ እንደምወደው መብል አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመሞቴ በፊት እንድመርቅህ የምወድደውን ዐይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ አብላኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሠርተህ አምጣልኝ፤ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅትህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ። |
እኅታቸው ርብቃንም መረቁአትና፥ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላት ሀገሮችን ይውረስ” አሉአት።
ያዕቆብም አባቱን አለው፥ “የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፤ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና ብለህ ተቀመጥ፤ ካደንሁትም ብላ።”
እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ ከአደንኸው እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አምጣልኝ” አለው። አቀረበለትም፤ በላም፤ ወይንም አመጣለት፤ እርሱም ጠጣ።
ወደ እርሱም ቀረበ፤ ሳመውም፤ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፤ ባረከውም፤ እንዲህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
እርሱም ደግሞ መብል አዘጋጀ፥ ለአባቱም አመጣ፤ አባቱንም፥ “አባቴ ተነሥ፤ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ልጅህ ከአደነው ብላ” አለው።
“እነሆ፥ አባትህ ለወንድምህ ለዔሳው፦ እንዲህ ሲለው ሰማሁ፤ ‘ሂድና ከአደንኸው መብል አዘጋጅተህ አምጣልኝ፤ ሳልሞትም በልች በእግዚአብሔር ፊት ልባርክህ።’
ወደ በጎቻችን ሄደህ ሁለት መልካም ጠቦቶች አምጣልኝ፤ እነርሱንም ለአባትህ እንደሚወደው መብል አደርጋቸዋለሁ፤
ዮሴፍም ለአባቱ ፥ “እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። ያዕቆብም፥ “እባርካቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅርብልኝ” አለው።
እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ናቸው፤ አባታቸውም ይህን ነገር ነገራቸው፤ ባረካቸውም፤ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸው።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእስራኤል መካከል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት ይሆን ዘንድ የተሠየመ ነው፤