ዘፍጥረት 27:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለውም፥ “አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” እርሱም፥ “እኔ ነኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም፣ “በርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም፣ “አዎን፤ ነኝ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለውም፦ “አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” እርሱም፦ “እኔ ነኝ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” ሲል እንደገና ጠየቀው፤ እርሱም “አዎ፥ ነኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለውም፦ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን? እርሱም፦ እኔ ነኝ አለ። |
እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ ከአደንኸው እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አምጣልኝ” አለው። አቀረበለትም፤ በላም፤ ወይንም አመጣለት፤ እርሱም ጠጣ።
እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፣ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፣
በፊቱም መልኩን ለወጠ፤ በዚያችም ቀን አመለጠ። በከተማውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፤ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር።
ዳዊትም ካህኑን አቤሜሌክን፥ “የተላክህበትን ነገርና የሰጠሁህን ትእዛዝ ማንም አይወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝዞኛል፤ ስለዚህም ‘ብላቴኖቼን በእግዚአብሔር መታመን’ በሚባለው እንዲህ ባለው ስፍራ እንዲሆኑ አዝዣቸዋለሁ።
አንኩስም ዳዊትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” አለው፤ ዳዊትም፥ “በይሁዳ ደቡብ፥ በያሴሜጋ ደቡብ፥ በቄኔዛውያን ደቡብ ላይ ዘመትን” አለው።