ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
ዘፍጥረት 24:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለኝ፦ አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል። መንገድህንም ያቀናል፤ ለልጄም ከወገኖች ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁ እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋራ ይልካል፤ ከገዛ ወገኖቼና ከአባቴ ቤት፣ ለልጄ ሚስት እንድታመጣለት መንገድህን ያቃናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፥ መንገድህንም ያቀናል፥ ለልጄም ከወገኖቼ ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንዲህ አለኝ ‘ዘወትር የማገለግለው እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤ ጒዞህም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፤ በዚህ ሁኔታ አንተም ከአባቴ ቤተሰብና ከዘመዶቼ መካከል ለልጄ ሚስት ልታጭለት ትችላለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለኝ፦ አካሄዴን በፊቱ ያደረግ ሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል መንገድህንም ያቀናም፤ ለልጄም ከወገኖቼ ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ |
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
ከአባቴ ቤት፥ ከተወለድሁባት ምድር ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፤ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።
ያዕቆብም ባረካቸው፤ እንዲህም አለ፥ “አባቶች አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ ደስ ያሰኙት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥
ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ ሄኖክም ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ።
እንደማዝዝህ የምታደርገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን፥ ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።
ሰሎሞንም አለ፥ “እርሱ በፊትህ በእውነትና በጽድቅ፥ በልብም ቅንነት ከአንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአባቴ ከባሪያህ ከዳዊት ጋር ታላቅ ቸርነት አድርገሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ ሰጥተህ ታላቁን ቸርነትህን አቈይተህለታል።
እንዲህም አለ፥ “የእስራኤል አምላክ አቤቱ! በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር አንተን የሚመስል አምላክ የለም፤ በፍጹም ልቡ በፊትህ ለሚሄድ ባሪያህ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥
“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መልካም ነገርም እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ አለቀሰ።
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
መልአኬንም ከአንተ ጋር በፊትህ እልካለሁ፤ ከነዓናዊውን፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውን፥ ኤዌዎናውዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ያወጣቸዋል።
መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉምን? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስ ለአገልግሎት ይላኩ የለምን?
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”