ዘፍጥረት 23:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመምሬ ፊት ያለው ባለ ድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻም ለአብርሃም ጸና፤ እርሻው፥ በእርሱም ያለ ዋሻው፥ በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው ዕንጨት ሁሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ፣ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለው የኤፍሮን ዕርሻ ቦታ ከነዋሻው በክልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ዓይነት ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ የተባለው የዔፍሮን ቦታ የአብርሃም ርስት ሆነ፤ ይህም ቦታ እርሻውን፥ በውስጡ ያለውን ዋሻና በእርሻው ክልል ውስጥ ያለውን ዛፍ ሁሉን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ከመምሬ በስተምሥራቅ ማክፌላ የተባለው የዔፍሮን ቦታ የአብርሃም ርስት ሆነ፤ ይህም ቦታ እርሻውን፥ በውስጡ ያለውን ዋሻና በእርሻው ክልል ውስጥ ያለውን ዛፍ ሁሉ ያጠቃልላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመምሬ ፊት ያለው ባለድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻ ለአብርሃም ጸና፤ |
ልጆቹ ይስሐቅና ይስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
ከአባቶችም ጋር በአንቀላፋሁ ጊዜ ከግብፅ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ፤ በአባቶችም መቃብር ትቀብረኛለህ።” እርሱም፥ “እንደ ቃልህ አደርጋለሁ” አለ። እርሱም፥ “ማልልኝ” አለው።
ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር መለሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት፤ እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።