Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 23:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በኬጢ ልጆ​ችና በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር በሚ​ገቡ ሁሉ ፊት ለአ​ብ​ር​ሃም ርስቱ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወደ ከተማው በር በመጡት ኬጢያውያንም ሁሉ ፊት የአብርሃም ንብረት መሆኑም ተረጋገጠለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሒታውያን ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ መሆኑ አረጋገጡለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በዚያም ተገኝተው የነበሩት ሒታውያን ሁሉ የአብርሃም ርስት መሆኑን አረጋገጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሻው በእርሱም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 23:18
8 Referencias Cruzadas  

ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥


ኤፍ​ሮ​ንም በኬጢ ልጆች መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ የኬጢ ሰው ኤፍ​ሮ​ንም የኬጢ ልጆ​ችና ወደ ከተማ የሚ​ገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአ​ብ​ር​ሃም እን​ዲህ ሲል መለ​ሰ​ለት፦


ከዚ​ህም በኋላ አብ​ር​ሃም ኬብ​ሮን በም​ት​ባል በመ​ምሬ ፊት በከ​ነ​ዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ሚስ​ቱን ሣራን ቀበረ።


ልጆቹ ይስ​ሐ​ቅና ይስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬ​ጢ​ያ​ዊው በሰ​ዓር ልጅ በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ቀበ​ሩት።


ኤሞ​ርና ልጁ ሴኬ​ምም ሄዱና ወደ ከተ​ማ​ቸው በር ደረሱ፤ ለከ​ተ​ማ​ቸ​ውም ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ነገሩ፦


በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር የሚ​ገቡ ሁሉ ኤሞ​ር​ንና ልጁን ሴኬ​ምን እሺ አሉ፤ ወን​ዶ​ችም ሁሉ የሰ​ው​ነ​ታ​ቸ​ውን ሸለ​ፈት ተገ​ረዙ።


የአ​ጎ​ቴም ልጅ አና​ም​ኤል፥ የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት የፈ​ረሙ ምስ​ክ​ሮች፥ በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ የተ​ቀ​መጡ አይ​ሁ​ድም ሁሉ እያዩ የው​ሉን ወረ​ቀት ለማ​ሴው ልጅ ለኔ​ርያ ልጅ ለባ​ሮክ ሰጠ​ሁት።


ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos