La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 21:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ር​ሃ​ምም በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን አም​ጥቶ ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ ሰጠው፤ ሁለ​ቱም ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ አብርሃም፣ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም በመካከላቸው የስምምነት ውል አደረጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፥ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሐላ አደረጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብረሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቤሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 21:27
15 Referencias Cruzadas  

ከአ​መ​ለ​ጡ​ትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕ​ብ​ራ​ዊው ለአ​ብ​ራ​ምም ነገ​ረው፤ እር​ሱም የኤ​ስ​ኮል ወን​ድ​ምና የአ​ው​ናን ወን​ድም በሆነ በአ​ሞ​ራ​ዊው የመ​ምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነ​ዚ​ያም ከአ​ብ​ራም ጋር ቃል ኪዳን ገብ​ተው ነበር።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህን ነገር ማን እን​ዳ​ደ​ረ​ገው አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ አን​ተም ደግሞ ምንም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም፤ እኔም ከዛሬ በቀር አል​ሰ​ማ​ሁም።”


አብ​ር​ሃ​ምም ሰባ ቄቦች በጎ​ችን ለብ​ቻ​ቸው አቆመ።


አሁ​ንም ና፤ አን​ተና እኔ ቃል ኪዳን እን​ጋባ፤ በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ይሁን።”


ትምህርት ገንዘብ ለሚያደርጓት የባለሟልነት ዋጋ ናት፥ ወደ ተመለሰችበትም መንገድን ታቀናለታለች።


ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።


በስውር ያለ ስጦታ ቍጣን ይመልሳል፥ ስጦታን የሚሸልግ ግን ጽኑ ቍጣን ያስነሣል።


ጻድ​ቃን ግን ጥበ​ብን ይመ​ክ​ራሉ፤ ምክ​ራ​ቸ​ውም ትጸ​ና​ለች።


ከመ​ን​ግ​ሥ​ትም ዘር ወስዶ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ አማ​ለ​ውም፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ኀያ​ላን ወሰደ፤


የማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ዝን​ጉ​ዎች፥ ፍቅ​ርም፥ ምሕ​ረ​ትም የሌ​ላ​ቸው ናቸው።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ሰውም እን​ኳን የጸ​ና​ውን ኪዳን አይ​ን​ቅም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ት​ምም።


ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።