Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 21:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ስለዚህ አብርሃም፣ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም በመካከላቸው የስምምነት ውል አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፥ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሐላ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አብ​ር​ሃ​ምም በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን አም​ጥቶ ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ ሰጠው፤ ሁለ​ቱም ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አብረሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቤሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 21:27
15 Referencias Cruzadas  

ከዚህም ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ይህን ነገረ፤ አብራም በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው በአሞራዊው መምሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ ነበር። መምሬ፣ ወንድሞቹ ኤስኮልና አውናን የአብራም የኪዳን አጋሮቹ ነበሩ።


አቢሜሌክም፣ “መቼም ይህን ድርጊት ማን እንደ ፈጸመ በበኩሌ አላውቅም፤ አንተም አልነገርኸኝም፤ ነገሩንም ገና አሁን መስማቴ ነው” አለው።


አብርሃም ከመንጋው ሰባት እንስት በጎች ለየ፤


በል አሁን ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ኪዳኑም በአንተና በእኔ መካከል ምስክር ይሁን።”


እጅ መንሻ ለሰጪው እንደ ድግምት ዕቃ ነው፤ በሄደበትም ቦታ ሁሉ ይሳካለታል።


እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤ ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች።


ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።


በስውር የተደረገ ስጦታ ቍጣን ያበርዳል፤ በጕያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቍጣን ጸጥ ያደርጋል።


ጨዋ ግን ሐሳቡም ጨዋ ነው፤ በጨዋነት ምግባርም ጸንቶ ይገኛል።


ከንጉሣውያን ቤተ ሰብ አንዱን ወስዶ ከርሱ ጋራ ውል አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው፤ የምድሪቱንም ታላላቅ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤


የማያስተውሉ፣ ውል የሚያፈርሱ፣ ርኅራኄ የሌላቸውና ጨካኞች ናቸው።


ወንድሞች ሆይ፤ ከሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደውን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብ፤ የሰው ኪዳን እንኳ አንድ ጊዜ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም በርሱ ላይ ሊጨምርበት እንደማይችል ሁሉ፣ በዚህም ጕዳይ ቢሆን እንደዚሁ ነው።


ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው፣ ከዳዊት ጋራ ኪዳን አደረገ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos