ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ዘፍጥረት 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳወጧቸውም፣ መልአኩ፣ “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ፈጥናችሁ ሽሹ፤ መለስ ብላችሁ ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ከረባዳው ስፍራ እንኳ ቆም አትበሉ፤ ወደ ተራራው ሽሹ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ራስህን አድን፥ ወደ ኋላህ አትይ፥ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኍላ እንዲህ አለው ራስህን አድን ወደ ኍላህ አትይ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ። |
ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ያም የጨው ሸለቆ የዝፍት ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራራማው ሀገር ሸሹ።
እንግዲህ ፍጠንና በዚያ ራስህን አድን፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።
ሎጥም ከሴጎር ወጣ፤ ከሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፤ በሴጎር መቀመጥን ፈርቶአልና እርሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ በዋሻ ተቀመጡ።
ማኅበሩንም፥ “ከእነዚህ ክፉዎች ሰዎች ድንኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ ለእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ” ብሎ ተናገራቸው።
ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማንም ዕርፍ ይዞ እያረሰ ወደ ኋላው የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይሆንም” አለው።
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበረና የሰሙትም ለእኛ አጸኑት።
ሳኦልም ዳዊትን ጠበቀው፤ በነጋው እንዲገድሉት መልእክተኞቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፤ ሚስቱም ሜልኮል፥ “በዚህች ሌሊት ነፍስህን ካላዳንህ ነገ ትገደላለህ” ብላ ነገረችው።