La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አብ​ራም ወደ ግብፅ ለመ​ግ​ባት በቀ​ረበ ጊዜ ሚስ​ቱን ሦራን እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መል​ካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ግብጽ ለመግባት ጥቂት ሲቀረው አብራም ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ውብ ሴት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ግብጽም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሣራን እንዲህ አላት፦ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አብራም ወደ ግብጽ ምድር ለመግባት በተቃረበ ጊዜ ሚስቱን ሣራይን እንዲህ አላት፤ “አንቺ በጣም ቈንጆ ሴት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ግብፅም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 12:11
14 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አብ​ራም ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ የግ​ብፅ ሰዎች ሴቲ​ቱን እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ቤት ባወ​ጣኝ ጊዜ አል​ኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድ​ር​ጊ​ልኝ፤ በገ​ባ​ን​በት ሀገር ሁሉ ወን​ድሜ ነው በዪ።’ ”


አብ​ር​ሃ​ምም ሚስ​ቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ስለ እር​ስዋ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉት “ሚስቴ” ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ የጌ​ራራ ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ላከና ሣራን ወሰ​ዳት።


ብላ​ቴ​ና​ይ​ቱም መል​ክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማ​ታ​ውቅ ድን​ግል ነበ​ረች። ወደ ውኃው ጕድ​ጓ​ድም ወረ​ደች፤ ውኃም ቀዳች፤ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም ሞልታ ወጣች።


የዚህ ስፍራ ሰዎች ለር​ብቃ ሲሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ እር​ስ​ዋም ውብ ነበ​ረ​ችና።


ልያም ዓይነ ልም ነበ​ረች፤ ራሔል ግን መልከ መል​ካም ነበ​ረች፥ ፊቷም ውብ ነበረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።


ቆን​ጆ​ዪ​ቱም እጅግ ውብ ነበ​ረች፤ ንጉ​ሡ​ንም ታቅ​ፈ​ውና ታገ​ለ​ግ​ለው ነበር፤ ንጉሡ ግን አያ​ው​ቃ​ትም ነበር።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


ልጅ ወን​ድሜ ለእኔ በዐ​ይ​ን​ጋዲ ወይን ቦታ እን​ዳለ እንደ አበባ ዕቅፍ ነው።


የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ።