ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖረው አምላክ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤትን ይሥራ፤
ዕዝራ 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡና ሰባቱ አማካሪዎቹ በእጅህ እንዳለችው እንደ አምላክህ ሕግ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ትጐበኝ ዘንድ አዝዘዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእጅህ በሚገኘው በአምላክህ ሕግ መሠረት፣ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም እንድትመረምር በንጉሡና በሰባት አማካሪዎቹ ተልከሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእጅህ እንዳለችው እንደ አምላክህ ሕግ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን እንድትመረምር በንጉሡና በሰባት አማካሪዎቹ ተልከሃል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ጋር እኔ ራሴ ከሰባቱ አማካሪዎቼ ጋር በአንድነት ያስተላለፍነውን ውሳኔ ለአንተ የተሰጠው የአምላክህ ሕግ በተግባር መፈጸሙን እየተመለከትህ፥ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያለውን ሁኔታ እንድትመረምር ልኬሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእጅህ እንዳለችው እንደ አምላክህ ሕግ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ትጐበኝ ዘንድ፥ |
ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖረው አምላክ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤትን ይሥራ፤
ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በጥሩ ድንጋይ ይሠራል፤ በቅጥሩም ውስጥ ልዩ እንጨት ይደረጋል፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል።
ስሙ በዚያ የሚኖር አምላክ ይህን ይለውጡ ዘንድ፥ በኢየሩሳሌም ያለውንም የእግዚአብሔርን ቤት ያፈርሱት ዘንድ እጃቸውን የሚዘረጉትን ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ ያጥፋ። እኔ ዳርዮስ ይህን አዝዣለሁ፤ በትጋት ይፈጸም።”
ይህን የእግዚአብሔርን ቤት ይሠሩ ዘንድ ለአይሁድ ሽማግሌዎች የምታደርጉትን፥ በወንዝ ማዶ ካለው ሀገር ከሚመጣው ግብር ከንጉሡ ገንዘብ ለእነዚህ ሰዎች ወጭውን በትጋት እንድትሰጡአቸው፥ ሥራም እንዳታስፈቱአቸው አዝዣለሁ።
ንጉሡና አማካሪዎቹም መኖሪያው በኢየሩሳሌም ለሆነው ለእስራኤል አምላክ በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብርና ወርቅ፥
በንጉሡ ፊት በሚመክሩትም፥ በኀያላኑም፥ በንጉሡ አለቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕረቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለችው በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁ፤ ከእኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእስራኤል አለቆቹን ሰበሰብሁ።
ንጉሡና አማካሪዎቹ፥ አለቆቹም፥ በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ ያቀረቡትን፥ ለአምላካችን ቤት የቀረበውን ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃውንም መዝኜ ሰጠኋቸው።