አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
ዕዝራ 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሁንም አንተ በወንዝ ማዶ ያለኸው የሀገሩ ገዥ ተንትናይ ደግሞ አሰተርቡዝናይ በወንዝ ማዶም ያሉ ተባባሪዎቻችሁ አፈርስካውያን ከዚያ ራቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም በኤፍራጥስ ማዶ አገረ ገዥ የሆንኸው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይና እናንተም በዚያ አውራጃ የምትገኙ ተባባሪዎቻቸው ሁሉ ወደዚያ አትድረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁንም በወንዝ ማዶ ያለውን አካባቢ ገዢ የሆንህ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይ በወንዝ ማዶም ያሉ ተባባሪዎቻቸው ባለ ሥልጣናት ከዚያ ራቁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳርዮስ የሚከተለውን መልእክት አስተላለፈ፦ “የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ ለሆንከው ለታተናይ፥ ለሸታርቦዝናይና በኤፍራጥስ ምዕራብ ለሚገኙ ተባባሪዎቻችሁ ሁሉ፦ ከቤተ መቅደሱ ራቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “አሁንም አንተ በወንዝ ማዶ ያለኸው የአገር ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ ሰተርቡዝናይ እና በወንዝ ማዶ ያሉ ተባባሪዎቻችሁ አፈርስካውያን ከዚያ ራቁ፤ |
አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
አምላኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገስን ይስጣችሁ፤ ያን ወንድማችሁንና ብንያምንም ይመልስላችሁ፤ እኔም ልጆችን እንዳጣሁ አጣሁ።”
አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓፊውም ሲምሳይ፥ የቀሩትም ተባባሪዎቻቸው፥ ዲናውያን፥ አፈርሳትካዋያን፥ ጠርፈላውያን፥ አፈርሳውያን፥ አርካውያን፥ ባቢሎናውያን፥ ሱስናካውያን፥ ዴሐውያን፥ ኤላማውያን፥
በዚያም ጊዜ በወንዝ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ አስተርቡዝናይ ተባባሪዎቻቸውም ወደ እነርሱ መጥተው፥ “ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘዛችሁ? የምትሠሩበትንስ ሥልጣን ማን ሰጣችሁ?” አሉአቸው።
በወንዙ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ አስተርቡዝናይ፥ ተባባሪዎቻቸውም፥ በወንዙ ማዶ የነበሩት አፈርስካውያንም ወደ ንጉሡ ወደ ዳርዮስ የላኩት የደብዳቤው ቃል ይህ ነበረ።
ንጉሡም ዳርዮስ እንደ ላከው ቃል፥ በዚያን ጊዜ በወንዝ ማዶ ያለ ገዥ ተንትናይ ደግሞ አስተርቡዝናይ ተባባሪዎቻቸውም እንዲሁ ተግተው አደረጉ።
ይህም የእግዚአብሔር ቤት ይሠራ ዘንድ ተዉ፤ የአይሁድም አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ይህን የእግዚአብሔርን ቤት በስፍራው ይሥሩ።
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።