ከጥሩ ወርቅም የተሠሩትን ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶቹንና ጭልፋዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም፥ ጽንሐሖችን፥ ለውስጠኛውም ቤት ለቅድስተ ቅዱሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅደሱም ደጆች የሚሆኑትን የወርቅ ማጠፊያዎች አሠራ።
ዕዝራ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕኖች፥ ሃያ ዘጠኝም ቢላዋዎች፥ ሠላሳ የወርቅ ዳካዎች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዕቃው ዝርዝር ይህ ነበር፤ የወርቅ ሳሕን 30 የብር ሳሕን 1,000 ዝርግ የብር ሳሕን 29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሰሐኖች፥ አንድ ሺህ የብር ሰሐኖች፥ ሀያ ዘጠኝ ቢላዋዎች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዕቃውም ዝርዝር እንደሚከተለው ነበር፦ ለመባ መሰብሰቢያ የሚሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ሳሕኖች 30 ለመባ መሰብሰቢያ የሚሆኑ ከብር የተሠሩ ሳሕኖች 1000 ሌሎች ልዩ ልዩ ሳሕኖች 29 ከወርቅ የተሠሩ ወጭቶች 30 ከብር የተሠሩ ወጭቶች 410 ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች 1000 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ፥ አንድ ሺህ የብር ሰሐኖች፥ ሀያ ዘጠኝ ቢላዎች፥ |
ከጥሩ ወርቅም የተሠሩትን ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶቹንና ጭልፋዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም፥ ጽንሐሖችን፥ ለውስጠኛውም ቤት ለቅድስተ ቅዱሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅደሱም ደጆች የሚሆኑትን የወርቅ ማጠፊያዎች አሠራ።
በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ወደ ካህኑ ኢዮአዳ ፊት አመጡ፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር ቤት ዕቃ፥ ለአገልግሎትና ለቍርባን ዕቃ፥ ለጭልፋዎችም፥ ለወርቅና ለብርም ዕቃ አደረጉት። በኢዮአዳም ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር።
ኪራምም ምንቸቶቹንና መጫሪያዎቹን፥ በመሠዊያው ቤት ያሉ ማንኪያዎችንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።
ዐሥሩንም የወርቅ ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ጽዋዎችን ሠራ።
ሃያም ባለ ሺህ ዳሪክ የወርቅ ጽዋዎች፥ ሁለትም እንደ ወርቅ የከበሩ ከጥሩና ከሚያንጸበርቅ ናስ የተሠሩ ዕቃዎችን መዝኜ በእጃቸው ሰጠሁ።
ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ይወስዱት ዘንድ ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ።
መባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤