ዕዝራ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9-10 የዕቃውም ዝርዝር እንደሚከተለው ነበር፦ ለመባ መሰብሰቢያ የሚሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ሳሕኖች 30 ለመባ መሰብሰቢያ የሚሆኑ ከብር የተሠሩ ሳሕኖች 1000 ሌሎች ልዩ ልዩ ሳሕኖች 29 ከወርቅ የተሠሩ ወጭቶች 30 ከብር የተሠሩ ወጭቶች 410 ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች 1000 Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የዕቃው ዝርዝር ይህ ነበር፤ የወርቅ ሳሕን 30 የብር ሳሕን 1,000 ዝርግ የብር ሳሕን 29 Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ቁጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሰሐኖች፥ አንድ ሺህ የብር ሰሐኖች፥ ሀያ ዘጠኝ ቢላዋዎች፥ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕኖች፥ ሃያ ዘጠኝም ቢላዋዎች፥ ሠላሳ የወርቅ ዳካዎች፥ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ፥ አንድ ሺህ የብር ሰሐኖች፥ ሀያ ዘጠኝ ቢላዎች፥ Ver Capítulo |
ሑራም በተጨማሪ ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችንና ማንቈርቈሪያዎችንም ሠራ፤ በዚህ ሁኔታም ሑራም ለንጉሥ ሰሎሞን እንዲሠራለት ቃል በገባለት መሠረት ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውለውን ዕቃ ሁሉ ሠርቶ ፈጸመ፤ የሠራቸውም ዕቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፦ ሁለት ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የሚገኙት የሳሕን ቅርጽ ያላቸው ሁለት ጒልላቶች፥ ሁለቱን ጉልላቶች ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ የሚገኙት በመርበብ አምሳል የተቀረጹት ሁለት ሰንሰለቶች፥ ጉልላቶቹን ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ በሁለት ዙር የተቀረጹ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ፍሬ ምስሎች፥ ዐሥሩ ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎች፥ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች፥ ትልቁ ገንዳ፥ በርሜሉን ደግፈው የያዙት የዐሥራ ሁለቱ በሬዎች ቅርጾች፥ ምንቸቶች፥ መጫሪያዎች፥ ሜንጦዎችና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ዕቃዎች በእጅ ጥበብ ሠራ። ታዋቂ የሆነው ሑራም በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ የሠራው ከተወለወለ ነሐስ ነበር።