ዘፀአት 9:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ እንዳልሞተ በአየ ጊዜ ልቡ ደነደነ፤ ሕዝቡንም አልለቀቀም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን ያጣሩ ዘንድ ሰዎች ልኮ ከእስራኤላውያኑ እንስሳት አንድም እንኳ አለመሞቱን ተገነዘበ። ያም ሆኖ ልቡ እንደ ደነደነ ስለ ነበር፣ ሕዝቡን አልለቀቀም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ላከ፥ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፥ ሕዝቡንም አልለቀቀም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ የሆነውን ሁሉ ለማጣራት ሰዎችን በላከ ጊዜ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ልቡን ስላደነደነ ሕዝቡን አለቀቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ላከ፤ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፤ ሕዝቡንም አልለቀቀም። |
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው።