Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ግን የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረውም፣ ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ጌታ ሙሴን እንደ ተናገረው ፈርዖን አልሰማቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ነገር ግን አሁንም እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ በማደንደን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሙሴ እንደ ተናገረ ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አላደመጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 9:12
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


“በዐ​ይ​ና​ቸው አይ​ተው፥ በል​ባ​ቸ​ውም አስ​ተ​ው​ለው እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ታወሩ፤ ልባ​ቸ​ውም ደነ​ደነ።”


እነሆ፥ የሚ​ወ​ድ​ደ​ውን ይም​ረ​ዋል፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ልቡን ያጸ​ና​ዋል።


ፈር​ዖ​ንም አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጄ​ንም በግ​ብፅ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሕዝ​ቤን በኀ​ይሌ በታ​ላቅ ፍርድ ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እኔ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጽ​ን​ቼ​አ​ለ​ሁና፥ ተአ​ም​ራቴ በእ​ነ​ርሱ ላይ በት​ክ​ክል ይመጣ ዘንድ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አል​ል​ቀ​ቀም።


ሙሴና አሮ​ንም እነ​ዚ​ህን ተአ​ም​ራ​ቶ​ችና ድን​ቆች ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ለመ​ል​ቀቅ እንቢ አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጸና፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አሳ​ደደ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ይ​ራ​ሩ​ላ​ቸው ፈጽ​መው እን​ዲ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይጋ​ጠሙ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ደ​ነ​ድኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን አጸና።


ፈር​ዖ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ እን​ዳ​ል​ሞተ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios