ዘፀአት 9:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውም፥ ነጐድጓዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደልን ጨመረ፤ እርሱና ሹሞቹም ልባቸውን አደነደኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ባየ ጊዜ እንደ ገና በደለ፤ እርሱና ሹማምቱ ልባቸውን አደነደኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውና ነጎድጓዱ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ ኃጢአትን ጨመረ፥ እርሱና አገልጋዮቹም ልባቸውን አደነደኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ግን ዝናቡ፥ በረዶውና ነጐድጓዱ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ እርሱና መኳንንቱ ልባቸውን በማደንደን እንደገና ኃጢአት ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ዝናቡ በረዶውም ነጎድጓዱም እንደ ተቍረጠ ባየ ጊዜ ኃጢያትን ጨመረ፤ እርሱና ባሪያዎቹም ልባቸውን አደነደኑ። |
ደግሞም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራቴን ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸናዋለሁ፤ ሕዝቡንም አይለቅቅም።
ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፤ እጁንም ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱም፥ በረዶውም ጸጥ አለ፤ ዝናቡም በምድር ላይ አላካፋም።
ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።
ግብጻውያንና ፈርዖንም ልባቸውን እንዳጸኑ ልባችሁን ለምን ታጸናላችሁ? በተዘባበቱባቸው ጊዜ ያወጡአቸው አይደሉምን? እነርሱም አልሄዱምን?