ዘፀአት 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና አሮንም ከፈርዖን ዘንድ ወጡ፤ ሙሴም ፈርዖን እንደ ቀጠረው ሰለ ጓጕንቸሮቹ መራቅ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴና አሮን ከፈርዖን ዘንድ ከተመለሱ በኋላ፣ በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ዘርጋ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ ተናካሽ ትንኝ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ በለው።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴና አሮን ከንጉሡ ፊት ወጥተው ሄዱ፤ በንጉሡ ላይ ያመጣቸውንም ጓጒንቸሮች ያስወግድለት ዘንድ ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴና አሮንም ከፈርዖን ዘንድ ወጡ። ሙሴም በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። |
ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ በታላቅ ኀይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር በአወጣኸው በሕዝብህ ላይ ለምን ተቈጣህ?
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ጓጕንቸሮቹን ከእኔ፥ ከሕዝቤም እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።
ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፤ እጁንም ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱም፥ በረዶውም ጸጥ አለ፤ ዝናቡም በምድር ላይ አላካፋም።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።
ደግሞ መልካሙንና ቅኑን መንገድ አሳያችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይንና እግዚአብሔርን ማገልገልን በመተው እርሱን እበድል ዘንድ እግዚአብሔር ይህን አያድርግብኝ።