La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “ወደ ፈርዖን ዘንድ ሄደህ፣ እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “እኔን ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ይዘህ እጅህን በፈሳሾቹ በወንዞቹና በኩሬዎቹ ላይ እጅህን ዘርጋ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አውጣ’ በለው።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ሄደህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 8:1
15 Referencias Cruzadas  

ፊን​ሐ​ስም ተነ​ሥቶ አዳ​ና​ቸው፥ ቸነ​ፈ​ሩም ተወ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “በእ​ው​ነት እኔ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እንደ ላክ​ሁህ ይህ ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ ሕዝ​ቡን ከግ​ብፅ በአ​ወ​ጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” አለው።


እነ​ር​ሱም ቃል​ህን ይሰ​ማሉ፤ አን​ተና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገ​ባ​ላ​ችሁ፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠር​ቶ​ናል፤ አሁ​ንም ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠዋ ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን ትሉ​ታ​ላ​ችሁ።


ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ አል​ሁህ፤ አን​ተም ልት​ለ​ቅ​ቃ​ቸው ባት​ፈ​ቅድ፤ እኔ የበ​ኵር ልጅ​ህን እን​ደ​ም​ገ​ድል ዕወቅ።”


ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”


እነ​ር​ሱም፥ “ቸነ​ፈር ወይም ሰይፍ እን​ዳ​ይ​ጥ​ል​ብን የሦ​ስት ቀን መን​ገድ በም​ድረ በዳ እን​ድ​ን​ሄድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ን​ሠዋ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ ጠራን” አሉት።


እን​ዲ​ህም ትለ​ዋ​ለህ፦ ‘የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነ​ሆም፥ እስከ ዛሬ አል​ሰ​ማ​ህም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወን​ዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈ​ጸመ።


ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ ሀገ​ር​ህን ሁሉ በጓ​ጕ​ን​ቸ​ሮች እመ​ታ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወ​ር​ዳል፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ጋይን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ጅህ ያለ​ውን ጦር በላ​ይዋ ዘርጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም የከ​በ​ቡ​አት ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ይነ​ሣሉ” አለው፤ ኢያ​ሱም በከ​ተ​ማዋ ላይ በእጁ ያለ​ውን ጦር ዘረጋ።