ዮሴፍም ለወንድሞቹ፥ “እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ ነውን?” አላቸው። ወንድሞቹም ይመልሱለት ዘንድ አልቻሉም፤ ደንግጠው ነበርና።
ዘፀአት 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶርም ተመለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞች እሄዳለሁ” አለው። ዮቶርም ሙሴን፥ “በደኅና ሂድ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ ዮቶር ተመልሶ ሄደና፣ “ወገኖቼ እስካሁን በሕይወት መኖራቸውን አይ ዘንድ ወደ ግብጽ ተመልሼ እንድሄድ እባክህ ፍቀድልኝ” አለው። ዮቶርም፣ “ሂድ፤ በሰላም ያግባህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ሄደ፥ ወደ አማቱ ወደ ይትሮ ተመለሰ፥ እርሱም፦ “እባክህን በግብጽ ወዳሉ ዘመዶቼ እንድመለስ እስካሁንም በሕይወት እንዳሉ ሄጄ እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። ይትሮም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የትሮ ተመልሶ ሄደና “በግብጽ ወደሚኖሩት ወገኖቼ ተመልሼ ሄጄ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። የትሮም ፈቅዶ “በሰላም ሂድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶር ተመለሰ፤ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንዳሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞቼ ልሂድ፤” አለው። ዮቶርም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው። |
ዮሴፍም ለወንድሞቹ፥ “እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ ነውን?” አላቸው። ወንድሞቹም ይመልሱለት ዘንድ አልቻሉም፤ ደንግጠው ነበርና።
ኤልሳዕም፥ “ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ተጠመቅ፤ ሰውነትህም ይፈወሳል፤ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ” ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ።
ሙሴም የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ በጎቹንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።
ከጥቂት ቀን በኋላም ጳውሎስ በርናባስን፦“እንግዲህስ እንመለስና የእግዚአብሔርን ቃል ባስተማርንባቸው ሀገሮች ያሉትን ወንድሞች እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው።
የወህኒ ቤቱ ጠባቂም በሰማ ጊዜ ሄዶ ገዢዎቹ “ይፈቱ” ብለው እንደ ላኩ ይህን ነገር ለጳውሎስና ለሲላስ ነገራቸው፤ “አሁንም ውጡና በሰላም ሂዱ” አላቸው።
የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው።