Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሙሴም ሄደ፥ ወደ አማቱ ወደ ይትሮ ተመለሰ፥ እርሱም፦ “እባክህን በግብጽ ወዳሉ ዘመዶቼ እንድመለስ እስካሁንም በሕይወት እንዳሉ ሄጄ እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። ይትሮም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ ዮቶር ተመልሶ ሄደና፣ “ወገኖቼ እስካሁን በሕይወት መኖራቸውን አይ ዘንድ ወደ ግብጽ ተመልሼ እንድሄድ እባክህ ፍቀድልኝ” አለው። ዮቶርም፣ “ሂድ፤ በሰላም ያግባህ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የትሮ ተመልሶ ሄደና “በግብጽ ወደሚኖሩት ወገኖቼ ተመልሼ ሄጄ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። የትሮም ፈቅዶ “በሰላም ሂድ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶ​ርም ተመ​ለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመ​ልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወን​ድ​ሞች እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ዮቶ​ርም ሙሴን፥ “በደ​ኅና ሂድ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶር ተመለሰ፤ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንዳሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞቼ ልሂድ፤” አለው። ዮቶርም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 4:18
11 Referencias Cruzadas  

ሙሴም የምድያን ካህን የሆነውን የአማቹን የይትሮን በጎች ያሰማራ ነበር፤ በጎቹን ከምድረ በዳው ማዶ ነዳቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


የእግዚአብሔር ስምና ትምህርት እንዳይሰደብ፥ በቀንበር ሥር ያሉ ባርያዎች ሁሉ ጌቶቻቸውን ታላቅ ክብር እንደሚገባቸው አድርገው ይቁጠሩአቸው።


የወኅኒውም ጠባቂ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ፤” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።


ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ፤” አለው።


ሴቲቱንም፦ “እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤” አላት።


ከዚያም ዔሊ፥ “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት።


ዮሴፍም ለወንድሞቹ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፥ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ አለን?” አለ። ወንድሞቹም፥ በፊቱ ደንግጠው ነበርና፥ ሊመልሱለት አልቻሉም።


ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀመጥ ፈቀደ፤ ልጁንም ጺጶራን ለሙሴ ሰጠው።


ኤልሳዕም “በሰላም ሂድ!” አለው፤ ንዕማንም ተሰናብቶ ሄደ። እርሱም ጥቂት ራቅ ብሎ እንደ ሄደ፥


ካህኑም፥ “የምትሄዱበት መንገድ በጌታ ፊት ነውና በሰላም ሂዱ” ብሎ መለሰላቸው።


ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ “‘ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠብ፤ ከበሽታህም ፈጽሞ ትነጻለህ’ ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው” ሲል አዘዘው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios