Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 16:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም በሰማ ጊዜ ሄዶ ገዢ​ዎቹ “ይፈቱ” ብለው እንደ ላኩ ይህን ነገር ለጳ​ው​ሎ​ስና ለሲ​ላስ ነገ​ራ​ቸው፤ “አሁ​ንም ውጡና በሰ​ላም ሂዱ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 የወህኒ ቤት ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ አዝዘዋል፤ ስለዚህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 የወኅኒውም ጠባቂ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ፤” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የወህኒ ቤት ጠባቂውም “እናንተ እንድትለቀቁ ባለሥልጣኖቹ ሰው ልከዋልና እንግዲህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ሲል ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 የወኅኒውም ጠባቂ፦ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 16:36
13 Referencias Cruzadas  

በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አያሌ ቀን ከተ​ቀ​መጡ በኋላ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ተሰ​ና​ብ​ተው በሰ​ላም ወደ ሐዋ​ር​ያት ተመ​ለሱ።


“ሰላ​ምን እተ​ው​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሰላ​ሜ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ዓለም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጠው አይ​ደ​ለም፤ ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ፍ​ሩም።


የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም ከእ​ን​ቅ​ልፉ በነቃ ጊዜ በሮች ሁሉ ተከ​ፍ​ተው አየ፤ ሰይ​ፉ​ንም መዝዞ ራሱን ሊገ​ድል ወደደ፤ እስ​ረ​ኞቹ ያመ​ለ​ጡት መስ​ሎት ነበ​ርና።


እርሱም “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሽ፤” አላት።


ኤል​ሳ​ዕም ንዕ​ማ​ንን፥ “በሰ​ላም ሂድ” አለው። ጥቂት መን​ገ​ድም ከእ​ርሱ ራቀ።


አሁ​ንም ተመ​ል​ሰህ በሰ​ላም ሂድ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች ዐይን ክፋት አታ​ድ​ርግ” አለው።


ዳዊ​ትም ያመ​ጣ​ች​ውን ከእ​ጅዋ ተቀ​ብሎ፥ “በሰ​ላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃል​ሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊት​ሽ​ንም እን​ዳ​ከ​በ​ርሁ ተመ​ል​ከቺ” አላት።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።


ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


ያም ካህን፥ “የም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነውና በሰ​ላም ሂዱ” አላ​ቸው።


ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶ​ርም ተመ​ለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመ​ልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወን​ድ​ሞች እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ዮቶ​ርም ሙሴን፥ “በደ​ኅና ሂድ” አለው።


በብ​ዙም ደብ​ድ​በው አሰ​ሩ​አ​ቸው፤ የወ​ህኒ ቤቱን ዘበ​ኛም አጽ​ንቶ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቃ​ቸው አዘ​ዙት።


በነጋ ጊዜም፥ ገዢ​ዎቹ፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ፈት​ታ​ችሁ ልቀ​ቋ​ቸው” ብለው ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios