“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ዘፀአት 34:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶች ልጆቻቸውምንም ከወንድ ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህንም ከወንድ ልጆቻቸው ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለወንዶች ልጆችህም ሴቶች ልጆቻቸውን ስታጭላቸውና እነዚህም ሴቶች ልጆች አምላኮቻቸውን በመከተል ሲያመነዝሩ፣ ወንዶች ልጆችህን ተመሳሳይ ድርጊት እንዲፈጽሙ ያነሣሧቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንድ ልጆችህ ብትወስድ፥ ሴቶች ልጆቻቸው አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ልጆችህን ከአምላኮቻቸው ጋር እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶች ብታደርጉ የእነዚያ ሴቶች ልጆች ጣዖት ማምለክን ስለሚከተሉ የእናንተንም ወንዶች ልጆች ጣዖት አምልኮን እንዲከተሉ ያደርጓቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴት ልጆቻቸውንም ከወንድ ልጆችህ ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ። |
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ንጉሡም ሰሎሞን ሴቶችን ይወድ ነበር፥ ከባዕዳን ሕዝብም የፈርዖንን ልጅ፥ ሞዓባውያትንና አሞናውያትን፥ ሶርያውያትንና ሲዶናውያትን፥ ኤዶማውያትንና አሞሬዎናውያትንም፥ ኬጤዎናውያትንም፦ ሚስቶችን አገባ።
ሌሎች ሠራዊትን እናመጣልሃለን፤ አንተም ቀድሞ በሞቱብህ ሠራዊት ምትክ ሹም፤ ፈረሱን በፈረስ ፋንታ፥ ሰረገላውን በሰረገላ ፋንታ ለውጥ፤ በሜዳውም እንዋጋቸዋለን፤ ድልም እናደርጋቸዋለን።” እርሱም ምክራቸውን ሰማ፤ እንዲሁም አደረገ።
ደግሞም በይሁዳ ተራሮች ላይ መስገጃዎችን ሠራ፤ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን እንዲያመነዝሩ አደረጋቸው፤ የይሁዳንም ሰዎች አሳታቸው።
አሁንም ትበረቱ ዘንድ፥ የምድሩንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ልጆቻችሁም ለዘለዓለም ይወርሱአት ዘንድ፥ ሴቶችን ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ፤ ሰላማቸውንና ደኅንነታቸውንም ለዘለዓለም አትሹ።
ለራሳቸውና ለልጆቻቸውም ሴቶች ልጆቻቸውን ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል፤ አስቀድሞም አለቆቹና ሹሞቹ በዚህ መተላለፍ መጀመሪያ ሆነዋል” አሉኝ።
የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን።
እነርሱንም ተቈጣኋቸው፤ ረገምኋቸውም፤ ከእነርሱም ዐያሌዎቹን መታሁ፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፥ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።
ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር የቃሉ መጀመሪያ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ሆሴዕን፥ “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታመነዝራለችና ሂድ፤ ዘማዊቱን ሴትና የዘማዊቱን ልጆች ለአንተ ውሰድ” አለው።
እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ፥ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ እናንተም ወደ እነርሱ፥ እነርሱም ወደ እናንተ ብትደራረሱ፥
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ መውደቂያና ወጥመድ፥ በእግራችሁም ችንካር፥ በዐይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንዳያጠፋቸው ራሳችሁ ዕወቁ።
አባቱና እናቱም፥ “ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለማግባት ትሄድ ዘንድ ከወንድሞችህ ሴቶች ልጆች፥ ከሕዝቤም ሁሉ መካከል ሴት የለችምን?” አሉት። ሶምሶንም አባቱን፥ “ለዐይኔ እጅግ ደስ አሰኝታኛለችና እርስዋን አጋባኝ” አለው።
የእስራኤልም ልጆች በከነዓናውያን፥ በኬጤዎናውያን፥ በአሞሬዎናውያን፥ በፌርዜዎናውያን፥ በኤዌዎናውያን፥ በኢያቡሴዎናውያንም መካከል ተቀመጡ።
ሴቶች ልጆቻቸውንም አገቡአቸው፤ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፤ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ።
ጌዴዎንም ምስል አድርጎ ሠራው፤ በከተማውም በኤፍራታ አኖረው፤ እስራኤልም ሁሉ ተከትሎ አመነዘረበት፤ ለጌዴዎንና ለቤቱም ወጥመድ ሆነ።