ዘፀአት 29:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልጆቹም በእርሱ ፋንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህን በመሆን እርሱን የሚተካውና በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚመጣው ወንድ ልጅ ሰባት ቀን ይለብሳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከልጆቹ በእርሱ ፈንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክህነቱ ሥልጣን ወራሽ በመሆን በተቀደሰው ስፍራ እኔን ለማገልገል ካህን ሆኖ ወደ ቅዱሱ ድንኳኔ የሚገባው የአሮን ልጅ እነዚህን ልብሶች ለሰባት ቀን ይልበስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከልጆቹም በእርሱ ፈንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው። |
“ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ።
በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ያችን ደዌ ይያት፤ እነሆም፥ ያች ደዌ በፊት እንደ ነበረች ብትሆን፥ በቆዳውም ላይ ባትሰፋ፥ ካህኑ ሰባት ቀን ደግሞ ይለየዋል።
የሚቀባውም፥ በአባቱም ፋንታ ካህን ሊሆን የሚካነው ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የተልባ እግር ልብስ ይልበስ።
ሙሴም የአሮንን ልብስ አወጣ፤ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ራስ ላይ ወረዱ።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።