Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 29:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከልጆቹ በእርሱ ፈንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ካህን በመሆን እርሱን የሚተካውና በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚመጣው ወንድ ልጅ ሰባት ቀን ይለብሳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የክህነቱ ሥልጣን ወራሽ በመሆን በተቀደሰው ስፍራ እኔን ለማገልገል ካህን ሆኖ ወደ ቅዱሱ ድንኳኔ የሚገባው የአሮን ልጅ እነዚህን ልብሶች ለሰባት ቀን ይልበስ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከል​ጆ​ቹም በእ​ርሱ ፋንታ ካህን የሚ​ሆ​ነው በመ​ቅ​ደስ ለማ​ገ​ል​ገል ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይል​በ​ሰው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ከልጆቹም በእርሱ ፈንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 29:30
17 Referencias Cruzadas  

ሰባት ቀን ከቈየም በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት።


ደግሞም ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ ዳግመኛም ወደ እርሱ ሳትመለስለት ቀረች።


ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።


የተቀደሰው የአሮን ልብስ ከእርሱ በኋላ ለልጆቹ ይሁን፥ ይኸውም እንዲቀቡበትና ክህነትን እንዲቀበሉበት ነው።


ለክህነት ሥርዓት የቀረበውን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ።


ለአሮንና ለልጆቹ እነዚህ ያዘዝሁህን ሁሉ አድርግ፤ ሰባት ቀን እጆቻቸውን ትቀድሳለህ።


ሰባት ቀን ለመሠዊያው ያስተሰርያሉ ያነጹታልም፥ እጃቸውን ይሞላሉ።


በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው መገታቱን ቢያይ፥ በቆዳውም ላይ ባይሰፋ፥ አሁንም ካህኑ ሰባት ቀን ይለየዋል።


በአባቱም ፈንታ ካህን ሆኖ ለማገልገል ተለይቶ የሚቀባው ካህን የተቀደሰውን የበፍታ ልብስ ለብሶ ያስተስርያል።


በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ።


አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ።


ሙሴም አሮን የለበሰውን ልብስ አወለቀ፥ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ።


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos