“አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አብዩድንም፥ አልዓዛርንም ኢታምርንም አቅርብ።
ዘፀአት 28:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ሁሉ ወንድምህን አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፤ እጆቻቸውንም ታነጻለህ፤ ትቀድሳቸውማለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህን ልብሶች ለአሮንና ለወንድ ልጆቹ ካለበስህ በኋላ ቅባቸው፤ ካናቸው፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ቀድሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን እነዚህን አልብሳቸው፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ እጆቻቸውንም ታነጻለህ፥ ትቀድሳቸዋለህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እነዚህን ልብሶች ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው፤ በክህነት ያገለግሉኝም ዘንድ የወይራ ዘይት በመቀባት የክህነትን ማዕርግ ትሰጣቸዋለህ፤ ትቀድሳቸዋለህም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ሁሉ ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ ትክናቸዋለህ፥ ትቀድሳቸውማለህ። |
“አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አብዩድንም፥ አልዓዛርንም ኢታምርንም አቅርብ።
የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ ልብሰ እንግድዓ፥ ልብሰ መትከፍ፥ ቀሚስም፥ ዥንጕርጕር እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያ፥ መታጠቂያም፤ እነዚህንም በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን፥ ለልጆቹም የተቀደሰ ልብስ ያድርጉ።
በመታጠቂያም ታስታጥቃቸዋለህ፤ ቆብንም ታደርግላቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዐትም ክህነት ይሆንላቸዋል፤ እንዲሁም የአሮንንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ።
አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፤ ካህናትም ይሆኑኛል። ይህም ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም የክህነት ቅብዐት ይሆንላቸዋል።”
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
የእግዚአብሔር የቅብዐት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አትውጡ” አላቸው። ሙሴም እንዳዘዛቸው አደረጉ።
በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፤ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ለካህናቱ እንዳስተሰረየ ለራሱም፥ ለሕዝቡም ያስተሰርያል።
ለቆሬም ለማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አላቸው፥ “ነገ እግዚአብሔር የእርሱ የሚሆኑትን፥ ቅዱሳንም የሆኑትን ያያል፥ ያውቃልም፤ የመረጣቸውንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀርባቸዋል።
ኦሪትስ የሚሞት ሰውን ሊቀ ካህናት አድርጋ ትሾማለች፤ ከኦሪት በኋላ የመጣው የእግዚአብሔር የመሐላ ቃሉ ግን ዘለዓለም የማይለወጥ ፍጹም ወልድን ካህን አድርጎ ሾመልን።
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።