ዘፀአት 25:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አብጅለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውስጡንና ውጪውም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በላዩ ላይ ዙሪያውን ሁሉ የወርቅ አክሊል አድርግለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውስጡንም ውጪውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አብጅለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት። |
በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው።
አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፤ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላ ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።
ለልብሰ እንግድዓውም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፤ ሁለቱንም ቀለበቶች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገን አድርጋቸው።
ወለሉንና የግድግዳውንም ዙሪያ፥ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የጥሩ ወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ።
በውስጥዋም የወርቅ ማዕጠንትና ሁለንተናዋን በወርቅ የለበጡአት፥ የኪዳን ታቦት፥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የለመለመችው የአሮን በትር፥ የኪዳኑም ጽላት ነበሩባት።