Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ርዝ​መት ሃያ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ ከዝግባ የተሠራውንም መሠዊያ በወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የቅድስተ ቅዱሳንም ርዝመት ሃያ ክንድ፥ ስፋቱም ሃያ ክንድ ቁመቱም ሀያ ክንድ ነበረ፤ በጥሩ ወርቅም ለበጠው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 6:20
10 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ያኖር ዘንድ በቤቱ ውስጥ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑን አበጀ።


በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ፊት ከዝ​ግባ መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ በጥሩ ወር​ቅም ለበ​ጠው።


የሠ​ራው ቤት ሁሉ እስከ ተፈ​ጸመ ድረስ ቤቱን ሁሉ በወ​ርቅ ለበ​ጠው፤ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ፊት የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ ሁሉ በወ​ርቅ ለበ​ጠው።


ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወ​ር​ቁን መሠ​ዊያ፥ የገ​ጹም ኅብ​ስት የነ​በ​ረ​በ​ትን የወ​ርቅ ገበታ፥


ቤቱ​ንም፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ መድ​ረ​ኮ​ቹ​ንም፥ ግን​ቦ​ቹ​ንም፥ ደጆ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበጠ፤ በግ​ን​ቦ​ቹም ላይ ኪሩ​ቤ​ልን ቀረጸ።


ሳን​ቆ​ቹን በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው፤ ቀለ​በ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም የመ​ወ​ር​ወ​ሪያ ቤት እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው ከወ​ርቅ ሥራ​ቸው፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው።


መሠ​ዊ​ያ​ውም ቁመቱ ሦስት ክንድ፥ ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም ሁለት ክንድ ሆኖ ከእ​ን​ጨት ተሠ​ርቶ ነበር፤ ማዕ​ዘ​ኖ​ቹም፥ እግ​ሩም፥ አገ​ዳ​ዎ​ቹም ከእ​ን​ጨት ተሠ​ር​ተው ነበር፤ እር​ሱም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለ​ችው ገበታ ይህች ናት” አለኝ።


በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ርዝ​መ​ቱን አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካና፥ “ይህ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነው” አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos