በየዓመቱም የመሬታችንን እህል ቀዳምያት፥ የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ቀዳምያት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
ዘፀአት 23:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የምድርህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቤት አምጣ። “ጠቦት ፍየልን በእናቱ ወተት አትቀቅል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ ጌታ አምላክህ ቤት አምጣ፤ ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በየዓመቱ ከምታመርቱት ምርት መጀመሪያ የደረሰውን በኲራት ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግን ወይም የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል። |
በየዓመቱም የመሬታችንን እህል ቀዳምያት፥ የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ቀዳምያት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወስዳለህ። ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ፥ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የአዝመራችሁን ቀዳምያት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።
በካህናቱም ድንበር አቅራቢያ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ፥ ወርዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ለሌዋውያን ይሆናል፤ ርዝመቱ ሁሉ ሃያ አምስት ሺህ፥ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል።
የበከተዉን ሁሉ አትብሉ፤ ይበላው ዘንድ በሀገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ወይም ለባዕድ ስጠው፤ አንተ ለአምላካህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።
አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ፍሬ ሁሉ ቀዳምያት ውሰድ፤ በዕንቅብም አድርገው፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደ መረጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።
ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።