ለራባቸውም ከሰማይ እንጀራን ሰጠሃቸው፤ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃን አወጣህላቸው፤ ትሰጣቸውም ዘንድ እጅህን የዘረጋህባትን ምድር ገብተው ይወርሷት ዘንድ አዘዝሃቸው።
ዘፀአት 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛንና ልጆቻችንን፥ ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሕዝቡ በዚያ ተጠምተው ስለ ነበር፣ በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እነርሱም፣ “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውሃ ጥም እንድናልቅ፣ ከግብጽ ለምን አወጣኸን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ ሕዝቡም በሙሴ ላይ አጉረመረሙ “እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብጽ አወጣኸን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ግን እጅግ ተጠምተው ስለ ነበር “ከግብጽ ምድር ያወጣኸን ለምንድን ነው? እኛንና ልጆቻችንን እንስሶቻችንንም ጭምር በውሃ ጥም ለመፍጀት ነውን?” እያሉ በሙሴ ላይ ማጒረምረማቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፦ እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኽን? ሲሉ በሙሴ ላይ አንጎራጎሩ። |
ለራባቸውም ከሰማይ እንጀራን ሰጠሃቸው፤ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃን አወጣህላቸው፤ ትሰጣቸውም ዘንድ እጅህን የዘረጋህባትን ምድር ገብተው ይወርሷት ዘንድ አዘዝሃቸው።
ያስተምራቸውም ዘንድ መልካሙን መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናህንም ከአፋቸው አልከለከልህም፤ ለጥማታቸውም ውኃን ሰጠሃቸው።
ሙሴንም አሉት፥ “በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸን? ከግብፅ ታወጣን ዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?
በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥ ቃሌንም ስላልሰሙ፥