ለራባቸውም ከሰማይ እንጀራን ሰጠሃቸው፤ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃን አወጣህላቸው፤ ትሰጣቸውም ዘንድ እጅህን የዘረጋህባትን ምድር ገብተው ይወርሷት ዘንድ አዘዝሃቸው።
ዘፀአት 16:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስከሚመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ወደ መኖሪያቸው ምድር እስኪመጡ ድረስ ለአርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ድንበር እስከሚደርሱ ድረስ መና በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ወደሚኖሩባት ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪደርሱ ድረስ ለአርባ ዓመት ሙሉ ይህን መና ተመገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ። |
ለራባቸውም ከሰማይ እንጀራን ሰጠሃቸው፤ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃን አወጣህላቸው፤ ትሰጣቸውም ዘንድ እጅህን የዘረጋህባትን ምድር ገብተው ይወርሷት ዘንድ አዘዝሃቸው።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አንከራተታቸው።
ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።
እነሆ፥ ምድሪቱን ሰጠኋችሁ፤ ግቡ፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ምድር ውረሱ።
አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም።
እግዚአብሔር ግን ታስተውሉ ዘንድ ልብን፥ ታዩም ዘንድ ዐይንን፥ ትሰሙም ዘንድ ጆሮዎችን እስከ ዛሬ ድረስ አልሰጣችሁም።
በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ዳግመኛ መና አላገኙም፤ በዚያው ዓመት የፊኒቆንን ምድር ፍሬ ሰበሰቡ።