ዘፀአት 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አንጐራጐሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳውም መላው የእስራኤል ልጆች ማኅበር በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በምድረ በዳ በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ምድረ በዳ ሁሉም ተባብረው በሙሴና በአሮን ላይ በማጒረምረም እንዲህ አሉ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በምድረ በዳ በሙሴና በአሮን ላይ አንጎራጎሩ። |
ሙሴንም አሉት፥ “በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸን? ከግብፅ ታወጣን ዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?
ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛንና ልጆቻችንን፥ ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ።
እነርሱም፥ “በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድለንም ዘንድ ሰይፍን በእጁ ሰጥታችሁታልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም” አሉአቸው።
በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥ ቃሌንም ስላልሰሙ፥