ሣራንም አላት “እነሆ፥ ለወንድምሽ አንድ ሺህ ምዝምዝ ብር ሰጠሁት፤ ይህም ለፊትሽ ክብር ይሁንሽ፤ በሁሉም እውነትን ተናገራት።”
ኤፌሶን 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሥራ ፍሬ ከሌላቸው፥ ሁለንተናቸውም ጨለማ ከሆነ ሰዎች ጋር አትተባበሩ፤ ገሥጹአቸው እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍሬ ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋራ ምንም ዐይነት ግንኙነት አይኑራችሁ፤ ይልቁን ግለጡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፤ ይልቁን ግለጡት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ብርሃን አውጥታችሁ አጋልጡት እንጂ ፍሬቢስ ከሆነ ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ |
ሣራንም አላት “እነሆ፥ ለወንድምሽ አንድ ሺህ ምዝምዝ ብር ሰጠሁት፤ ይህም ለፊትሽ ክብር ይሁንሽ፤ በሁሉም እውነትን ተናገራት።”
እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፥ በበርም ለሚገሥጸው አሽክላ የሚያኖሩ፥ ጻድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱ ናቸው።
“ወንድምህን አትበድለው፤ በልብህም አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኀጢአት እንዳይሆንብህ ባልንጀራህን የምትነቅፍበትን ንገረው፤ ገሥጸውም።
ዮሐንስም የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሄሮድስ ያደርገው ስለነበረው ክፉ ነገር ሁሉ ይገሥጸው ነበር።
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን፥ መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን እንድታውቁባቸው እማልዳችኋለሁ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤
ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።