አቤቱ፥ ከተግሣጽህ፥ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።
ኤፌሶን 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክርስቶስን ፍቅር ለመረዳት፥ በእግዚአብሔር ፍጹምነት በሁሉ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ እግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ፣ ከመታወቅ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ታውቁም ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ድረስ እንድትሞሉ፥ እውቀትን የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር እንድታውቁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ከሰው ዕውቀት በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር እንድታውቁ በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ለመሞላትም እንድትበቁ እጸልያለሁ። |
አቤቱ፥ ከተግሣጽህ፥ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ነውን? ኀዘን ነውን? ስደት ነውን? ራብ ነውን? መራቆት ነውን? ጭንቀት ነውን? ሾተል ነውን?
ከክርስቶስ ጋርም ተሰቀልሁ፤ ሕይወቴም አለቀች፤ ነገር ግን በክርስቶስ ሕይወት አለሁ፤ ዛሬም በሥጋዬ የምኖረውን ኑሮ የወደደኝን ስለ እኔም ራሱን አሳልፎ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እኖራለሁ።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
ወንዶችም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት፥ ራሱንም ስለ እርስዋ ቤዛ አድርጎ እንደ ሰጠላት ሚስቶቻቸውን ይውደዱ።
ስለ እናንተ ይህን ላስብ ይገባኛል፤ በምታሰርበትና በምከራከርበት፥ ወንጌልንም በማስተምርበት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባበራችሁ በልቤ ውስጥ ናችሁና።
ሁሉ የሚገኝባት፥ ከልቡናና ከአሳብ ሁሉ በላይ የምትሆን የእግዚአብሔር ሰላም በኢየሱስ ክርስቶስ ልባችሁንና አሳባችሁን ታጽናው።
ወደ እግዚአብሔር በሚገባችሁ ትሄዱ ዘንድ፥ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ፥ እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ፥ በሁሉ ደስ ታሰኙት ዘንድ።
እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።