ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣም።”
ኤፌሶን 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሱስ ክርስቶስም አስነሥቶ በሰማያት ከእርሱ ጋር አኖረን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ከክርስቶስ ጋራ አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከርሱ ጋራ አስቀመጠን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ከክርስቶስ ጋር አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት ከእርሱው ጋር ከሞት አስነሥቶ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። |
ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣም።”
ጌታቸው በመጣ ጊዜ እንዲህ ሲያደርጉና ሲተጉ የሚያገኛቸው አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ወገቡን ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ እየተመላለሰም ያገለግላቸዋል።
እኔን የሚያገለግለኝ ካለ ይከተለኝ፤ የሚያገለግለኝ እኔ ባለሁበት በዚያ ይኖራልና፤ እኔን የሚያገለግለኝንም አብ ያከብረዋል።
ከሄድሁና ቦታ ካዘጋጀሁላችሁም ዳግመኛ እመጣለሁ፤ እናንተም እኔ በአለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ከጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ በኤፌሶን ላሉ ቅዱሳን፥
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።