ኤፌሶን 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ የጥፋት ልጆች ሆንን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንን ምኞት እያረካን፣ መንገዱንም እየተከተልን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም የቍጣ ልጆች ነበርን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነዚህም ልጆች መካከል እኛም ሁላችን፥ የሥጋችንንና የህዋሳቶቻችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበር፤ ደግሞም እንደ ሌሎቹ በባሕርያችን የቁጣ ልጆች ነበርን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛም ሁላችን ከዚህ በፊት በእነርሱ መካከል የሥጋችንን ፈቃድና የአእምሮአችንን ሐሳብ እየተከተልን በሥጋችን ምኞት እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም በተፈጥሮአችን በእግዚአብሔር ቊጣ ሥር ነበርን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። |
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም ስለ ኀጢአታችን ለሞት አሳልፎ ሰጠው።
እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና።
ሕግ የሌላቸው አሕዛብስ እንኳ ለራሳቸው ሕግ ይሠራሉ፤ ራሳቸው ለራሳቸው ሕግን ይደነግጋሉ፤ በሕጋቸው የታዘዘውንም ያደርጋሉ።
እና የእግዚአብሔር ጠላቶቹ ስንሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታረቀን በኋላም በልጁ ሕይወት እንዴት የበለጠ ያድነን!
በእኔ ማለት በሥጋዬ መልካም ነገር እንደማይኖር አውቃለሁ፤ መልካም ሥራ ለመሥራት መሻቱስ በእኔ ዘንድ አለ፤ በጎ ምግባር መሥራት ግን የለኝም።
እግዚአብሔርም ኀይሉን የሚገልጽበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ፥ ትዕግሥቱን ካሳየ በኋላ ለማጥፋት የተዘጋጁትን ቍጣውን የሚገልጽባቸውን መላእክት ያመጣል።
ማን ይመረምርሃል? የምትታበይስ በምንድን ነው? ከሌላ ያላገኘኸው አለህን? ያለህንም ከሌላ ካገኘህ እንዳላገኘ ለምን ትኮራለህ?
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለሆን ራሳችንን እናንጻ፤ ሥጋችንን አናርክስ፤ ነፍሳችንንም አናሳድፍ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት የምንቀደስበትን እንሥራ።
ነገር ግን ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ይሆን ዘንድ፥ ያመኑትም ያገኙት ዘንድ፥ መጽሐፍ ሁሉን በኀጢአት ዘግቶታል።
ይኸውም ቀድሞ በዚህ ዓለም ሥርዐት፥ አሁን በከሓድያን ልጆች የሚበረታታባቸውና፥ በነፋስ አምሳል የሚገዛቸው አለቃ እንደ ነበረው ፈቃድ ጸንታችሁ የነበራችሁበት ነው።
ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
ምንዝር የሞላባቸው ኀጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።
ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤ ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል።